0

ውሸት ባንዋሽስ?

ውድ አንባቢዎቻችን፣

የተለያዩ ድረገጾች የኛን ጽሑፎች የራሳቸው አስመስለው እንደሚያቀርቡ እናውቃለን። ለምን ይዋሻል? ፌስቡክ ላይም የኛን ስራዎች የራሳቸው አስመስለው የሚያቀርቡ ቁጥራቸው ትንሽ አይደለም። የማናይና የማንሰማ መስሏቸው ከሆነ በጣም ተሳስተዋል። እዚህ እየመጡ “ሀገር አጠፋቹ፣ ገደል ግቡ” እያሉ ይሳደቡና ዞር ብለው ደግሞ እኛ የምንጽፈውን እንዳለ ገልብጠው እነሱ የጻፉት አስመስለው ያቀርባሉ። ሼም የለም እንዴ?

ለማነኛውም እኛ መጻፋችንን አናቆምም። ለምታነቡን ምሳጋናችን ከፍ ያለ ነው። አንብባችሁም ለጓደኞቻችሁ የምታካፍሉትንም እንወዳችኋለን። የማይመቹን ውሸታሞችና አስመሳዮች ብቻ ናቸው።

ስለወሲብ ለምን ተጻፈ ብላቹ የምታለቃቅሱብን ደግሞ ቆይ ግን እናንተ እንዴት ይህን ገጽ ልታገኙት ቻላችሁ? ስለወሲብ መጎልጎል ለምን አስፈለጋችሁ? እስኪ አጉል አናስመስል! ከመጋረጃ ጀርባ የምታደርጉትን ለመሸወድ የምትሞክሩት ፈጣሪያችሁ በደንብ ያውቃል። እዚህ መጥታችሁ ንጹህ እንደሆነ ሰው አታለቃቅሱ። እንተዋወቃለን።

የኛ ዓላማ ስለወሲብ ሰውን ማንቃት ነው። እኛ ያልባለገን አባልገን አናውቅም። ሁላችንም ቅልጥ ያልን ባለጌዎች ነን። መባለጋችን ካልቀረ ደግሞ በመማማር እንባልግ። ለጤናችንም ሆነ ለእርካታችን ስንል በራሳችን ቋንቋ ስለወሲብ ጠለቅ ብለን ማወቅና ማሳወቅ አይከፋም። እኛን ከመውቀሳችሁ በፊት በመጀመሪያ ደረጃ ወደኛ ድረገጽ የሚመጣው ሰው ጉግል ላይ ምን ሲፈልግ እንደሆነ እወቁ። የሚከተሉት ቃላት ተደጋግመው የሚጠቀሱ ናቸው።

እምስ
ወሲብ
ሴክስ
ብዳኝ
ወሲብና መሳሳም
ኦራል ሴክስ
ቁላ
እምስ መላስ
መባዳት ፈልጋለሁ
ቁላ ና እምስ
አናል ሴክስ

እነዚህን ነገሮች የሚፈልጉ ወገኖች እስካሉ ድረስ መጻፋችንን አናቆምም። ቢያንስ ስለመብዳትና መባዳት ብቻ ሳይሆን ስለጤና ጥበቃም መረጃን ሰጥተን እንሸኛቸዋለን። ስለዚህ ወግ አናጥብቅ። ያልተመቸው ካለ እጁን ያውጣ።

እናመሰግናል!

Dear Readers,

We know a lot of websites use our materials without giving us credit. There have also been some fake Facebook pages that were created using our name. We want our readers to know that we will soon create an official Facebook page and we will let you know here when it is ready! We are happy you are sharing what we write. But we are also aware of those who are lying on Facebook, pretending that they are behind this page. You don’t have to lie. Just learn to give credit and stay real!

Eroticalitopia
The 1st and
The No. 1 WESIB Blog
in Amharic

0

“ፍቅረኛዬን ከሌላ ሴት ጋር ያዝኩት”

ሰላም አንባቢዎች! ሊሊ የምትባል አንባቢያችን የሚከተለውን መልዕክት ልካልን ነበር። እኛም ምላሽ አዘጋጅተናል።

ሊሊ የጻፈችልን መልዕክት ባጭሩ፣

“ከፍቅረኛዬ ጋር አብረን ከሆንን አምስት አመት ሆኖናል። ከሁለት አመት ወዲህ ግን ልቤ ጠርጥሮታል። ከአንድ ወር በፊት አንድ ሁለት ቀን ስልክ ስደውልለት አያነሳም። አንድ ቀን መንገድ ላይ ታክሲ ስጠብቅ ከሆነች ሴት ጋር በመኪና ሲያልፍ አየሁት። ከሶስት አመት በፊት ከዚህች ሴት ጋር አይቼው ነበር። እናም ስንገናኝ እውነቱን እንዲነግረኝ ጠየኩት። እሺ ብሎ ነገረኝ። የሚያውቃት ከ12 አመት በፊት እንደነበር ነገረኝ። ወሲብ እንደፈፀሙና ለገንዘብ ብሎ እንደቀረባት ነገር ግን ወሲብ ላይ እንደማትመቸውም ነገረኝ። ባለትዳርና የልጆች እናት ናት። የሚገርመው ዕድሜው ከ46 እስከ 50 ይሆናል። ሥራው መሐንዲስ ሲሆን መኖርያ ቤትም አለው። ስለዚህ ሰው ምን ትመክሩኛላችሁ?”

ውድ ሊሊ፣

በመጀመርያ ስለጻፍሽልን ከልብ እናመሰግናለን። ከፍቅረኛሽ ጋር ያለሽ ግንኙነት ጥሩ ሁኔታ ላይ አለመሆኑን እያዘንን ምክራችን የሚከተለው ይሆናል።

ከፍቅረኛሽ ጋር አምስት አመት ብትኖሩም እንደተረዳነው ከሆነ ጊዜውን ያሳለፋችሁት ብዙም ሳትተዋወቁ ነው። ሰፊ የሆነ የዕድሜም ልዩነት በመሐላቹ ያለም ይመስለናል። ምክንያቱም ዕድሜው ከ46 እስከ 50 ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ መሆኑ እንዳስገረመሽ ጽፈሻል። ሌላው የተገነዘብነው ነገር ከእሱ ጋር አብረሽ እንደማትኖሪ ነው። የራሱ ቤትና ሥራ እንዳለው ነገርሽናል።

የኛ መላምት ይህን ይመስላል።

1 – ፍቅረኛዬ ያልሽው ሰው ሌላን ሴት ሳይሆን በአንቺ ላይ የደረበው አንቺን ለ5 አመት በሌላ ሴት ላይ መደረቡን

2 – ያቺንም ሴት ሳያቆም እንደሚያያት

3 – አንቺ የማታውቂያት የትዳር ጓደኛም ልትኖረው ትችላለች። ቤቱ ሄደሽ ታውቂያለሽ? ብቻውን ነው የሚኖረው? ለገንዝብ ብዬ ነው የቀረብኳት ያላት ሴት ሚስቱ ብትሆንስ? እሱን በመጠይቅ ብቻ ሳይሆን በሌላ መንገድ በደንብ ልታረጋግጪ የምትችይበት ሁኔታ አለ?

4 – የዛሬ 12 ዓመት በጥቅም የተዋወቃትን ሴት አሁን ድረስ አንቺን በጎን አስቀምጦ የሚያያት ለምንድነው? እውነት እንደሚለው በወሲብ ስለማታረካው ነበር የራቃት ወይንስ አሁንም ለጥቅሙ ሲል ይፈልጋታል?

5 – ሰውየው አንቺን መተው አይፈልግም። ያቺንም መተው አይፈልግም። ለአምስት አመት ደብቆሽ የኖረውን ጉዳይ አሁን ነግሮሻል። ለምን ይመስልሻል?

6 – አንቺ ከሱ የምታገኝው ጥቅም ምንድነው? በተለይ በዕድሜ ብዙ የምትለያዩ ከሆነና በግልጽ ከሌላ ሴት ጋር ለጥቅም ብሎ እንደሚተኛ እየነገረሽ አብረሽው ለመኖር የምትፈልጊበት ምክንያት ምንድነው? ከሱ የተሻለ ወንድ አላገኝም ብለሽ ነው? ስለምታፈቅሪው ነው? ፍቅር እኮ ታድያ እኩል መሆን አለበት።

7 – አንቺ እንደምታፈቅሪው እሱ ካላፈቀረሽና ካላከበረሽ የፍቅር ትርጉሙ ምንድነው?

8 – አንቺ እሱን የምታይው በፍቅረኛ ዓይን ሲሆን እሱ ግን አንቺን የሚያይሽ በውሽማ ዓይን ነው። በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት እንደ ውቅያኖስ የሰፋ ነው።

እንደኛ ዕምነት ከሆነ የሚከተሉትን ብትፈጽሚ ራስሽን ከብዙ ራስምታትና አላስፈላጊ ችግር ውስጥ ነፃ ታወጫለሽ።

1 – ከዚህ ግንኙነት ምንድነው የምትፈልጊው? ራስሽን በደንብ ጠይቂው። የወደፊት ዓላማሽ ምንድነው? ከሱ ጋር ተጋብቶ መኖር?

2 – የእሱስ አላማ ምንድነው? አምስት አመት አብራችሁ አሳለፋችሁ። ከዚህ በኋላ ያለውንስ ጊዜ እንዴት ማሳለፍ ነው የሚፈልገው? ካንቺ ጋር ትዳር መስርቶ የመኖር ዓላማ አለው? ከሆነ ደግሞ መቼ? ቁርጥ ያለ ጊዜና ሰዓት ልታገኚ ይገባል። ዝም ብሎ ተስፋ ብቻ ሳይሆን።

3 – ከሴትዮዋ ጋር አሁን ያለው ግንኙነት ምንድነው? እንዴትስ ልታረጋግጪ ትችያለሽ?

4 – ከሴትዮዋ ጋር ዛሬ ምንም ግንኙነት የለኝም ቢልሽ ምን ማስተማመኛ አለሽ? እሱ ስላለሽ ብቻ እንደሞኝ ልታምኝው ነው?

5 – በዕድሜ ስለሚበልጥሽ እስከዛሬ አታሎሽ ሊሆን ይችላል። ዳግም ላለመታለል ልትወስጂው የምትችይው እርምጃ ምንድነው? አንዴ ያማገጠ ሁሌም አማጋጭ መሆኑን አትዘንጊ።

ለእነዚህ ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ ካገኘሽ በኋላ ውሳኔ ላይ የመድረስ ፋንታ ያንቺ ይሆናል። እኛ ተለያዩ ለማለት ይከብደናል። ነገር ግን ግንኙነታችሁ አሁን ባለበት ሁኔታ ጤናማ አለመሆኑንና መፍትሄ ከሌለው ብትለያዩ ጥሩ ነው የሚል ዕምነት አለን። ላንቺ የሚሆን ወንድ አይጠፋም። በተለይ ወጣት ከሆንሽ፣ ገና ብዙ ጊዜ ስላለሽ፣ አማርጠሽ፣ ኮርተሽ የሚያፈቅርሽንና “ካንቺ ሌላ ሴት ለምኔ?!” የሚል ወንድ ታገኛለሽ። ወጣት ባትሆኚም የሚመጥንሽን አፍቃሪ ወንድ አታጭም። በራስሽ የምትተማመኚ ከሆንሽ በየትኛውም የዕድሜ ክልል ውስጥ ብትሆኚ የሚንገበገብልሽን ወንድ አታጭም። ካልተገኘም፣ ፍቅረኛዬ የምትይውን ሰው ከሌላ ሴት ጋር ከምትጋሪ፣ መጋራትን እንደ ምርጫ የማታዪ ከሆነ፣ የሚሆንሽ ሰው እስኪገኝ ድረስ ለብቻሽ መኖር የተሻለ አማራጭ ነው። ከዚህ ፍቅረኛሽ ጋር መለያየቱ ሊከብድሽና መጥፎ ሐዘን ውስጥ ሊከትሽ ይችላል። ግን በህይወትሽ ደስተኛ ለመሆን የግድ ወንድ ያስፈልግሻል ማለት አይደለም። በተጨማሪ ደግሞ እዚህም፣ እዚያም እንደውሻ ሲቀላውጥ በወሲብ የሚተላለፍ በሽታ ቢያሸክምሽስ? ራስሽን ልትጠብቂ ይገባል። ከራስ በላይ ንፋስ ነው።

ምርጫው ያንቺ ነው። ተከብረሽ አንቺን ብቻ ከሚመርጥ ሰው ጋር መኖር ወይም ሳትከበሪ ከሌላ ሴት ጋር እያፈራረቀ ከሚበዳሽ ወንድ ጋር መኖር። ነፃነት ወይስ ባርነት?

– ነፂ

0

“ምን ይሻለኛል?”

ሰላም፣ ሰላም ውድ አንባቢዎች!

ሳንጦምር 3 ዓመት አለፈን። በጣም ጠፋንባችሁ አይደል? እንደናፈቃችሁን ተስፋ እናደርጋለን። ይህን ጦማር ስንጀምር ሰባት ሰዎች ነበርን። ዛሬ ግን በተለያዩ ምክንያቶች ቁጥራችን ቀንሶ ሦስት ብቻ ቀርተናል።

ዴቭ፣ ነፃነትና ሶፊ።

ከብዙ ቆይታ በኋላ ለመጦመር ስንመለስ በመጀመርያ ያደረግነው እናንተ የተዋችሁልን ጥያቄዎች ማንበብ ነበር። እነዚህን ጥያቄዎች ተከፋፍለን ምላሽ ይዘን ቀርበናል።

ዛሬ የምጽፍላችሁ ሶፊ ነኝ። በርዕሱ የምታዩትን ጥያቄ ለመመለስ ብቅ ብያለሁ።

አንድ አንባቢያችን “ሴት ባየሁ ቁጥር ቁላየ እየቆመ አስቸግሮኛል። ምን ይሻለኛል?” የሚል ጥያቄ አንስቷል።

የኔ መልስ አጭር ነው።

1ኛ – የጻፍከው ነገር ለሴቶች ስድብ ነው። ምን ያህል ለሴት ልጅ ክብር እንደሌለህ ያሳያል። የሴትን ልጅ ባየህ ቁጥር ቀድሞ የሚታሰብህ ወሲብ ከሆነ ችግር አለብህና የስነልቦና ህክምና ጠይቅ። የሴት ልጅ ያንተ ቁላ ማስነሻ ዕቃ አይደለችም። ክብር ያላት ፍጡር ነች። ስለዚህ ራስህን ገምግም።

2ኛ – ቁላህን ቆንጥጠው። ስሜትህን ልትገዛው እንጂ ስሜትህ ሊገዛህ አይገባም። በጭንቅላትህ ሳይሆን በቁላህ ብቻ እያሰብክ ስለሆነ ራስህን ግዛ።

3ኛ – እህት አለህ? የሴት ዘመድስ አለህ? እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ። የሆነ ወንድ “እነዚህ ዘመዶችህን ባየሁ ቁጥር ቁላዬ ይቆማልና ምን ላድርግ” ቢልህ ምን አድርግ ብለህ ትመክረዋለህ? ያዙኝ፣ ልቀቁኝ፣ እገድለዋለሁ እንደምትል እርግጠኛ ነኝ። ያንተንም ሁኔታ በዚሁ መልኩ እየውና ራስህን ታዘበው።

በነገራችን ላይ እንዳንተ ያሉ ወንዶች እንደዚህ ዓይነት ሐሳብ የምታስቡት ሴትን ልጅ ከወሲብ ማርኪያነት ውጭ አርቆ የሚያስብ አዕምሮ ስለሌላችሁ ነው። ያቺ የምታያትና ቁላህ የሚቆምላት ሴት ግን የሌላ ሰው እህት፣ እናት፣ አክስት፣ ሚስት፣ ፍቅረኛ፣ ጓደኛ፣ ጎረቤት፣ ልጅ ነች። በወሲብ ዕቃነቷ ሳይሆን በሰውነቷ እያትና አክብራት። በህይወቷ ለማሳካት የምትፈልጋቸው ነገሮች ምን እንደሆኑ ለማወቅ ጣር። ያቺ ሴት ከወሲብ ቀስቃሽ ገላዋ በፊት የሚያስብ አዕምሮና የሚያፈቅር ልብ የያዘች ሰው መሆኗን ተረዳ። ያኔ በሰውነቷ ልትተዋወቃት ትችላለህ። ሴትነቷን ካከበርክ ማን ያውቃል ወዳህ ተዋዳችሁ ልብህ እስኪወልቅ ድረስ ልተበዳህ ትችላለች። ቅድሚያ ግን ማንነቷን ከወሲብ ጋር ብቻ አታያይዝ።

4ኛ – የምታስበው ነገር ሁሉ ወሲብ ብቻ ከሆነ የሴተኛ አዳሪዎች አሉልህ። እነሱንም ቢሆን ልታከብራቸው ይገባል። ሰውነታቸውን ስለሚሸጡልህ ከሰውነት በታች ልታያቸው አይገባም። ኤድስንና ሌሎች በወሲብ የሚተላለፉ በሽታዎችንም አትርሳ!

ህይወትህን ስለወሲብ ብቻ እያሳሰብክ ቀፎ አታድርገው።

ሶፊ