ወሲብና ትዳር

ከጋብቻ በኋላ ወሲብ ለብዙዎች ቀዝቃዛ ወላፈን ነው። የጋብቻ ቀለበት አጠለቃችሁ ማለት ወሲብን ልጅ ለመውለድ ብቻ ተጠቀሙበት ማለት አይደለም። ከጋብቻ በፊት በቀን ሦስት፣ አራት ጊዜ ሲደረግ የነበረው ወሲብ፤ ከጋብቻ በኋላ በቀን አንዴ፣ በሳምንት ሁልቴ፣ በሁለት ሳምንት አንዴ፣ በወር አንዴ፣ በስድስት ወር አንዴ፣ በአመት አንዴ እያለ ደብዛው ይጠፋል። የልጆች ኃላፊነትና ሥራ ሲደራረቡ የወሲብ ጣሙ መረሳት ይጀምራል።

ብዙ ወንዶች ካገቡ የወሲብ ጥማታቸው ላይ ቀዝቃዛ ውሃ እንደሚፈስበት አድርገው ያስባሉ። ነገር ግን ጋብቻ የወሲብን ወላፈን የሚያጠፋ ቀዝቃዛ ውሃ አይደለም። የወሲብ ጥማት ሳይበርድ ለብዙ ዓመታት ቀጣይነት ያለው እንዲሆን የባልና ሚስትን ያላሳለሰ ጥረት ይጠይቃል። ያ ካልሆነ በሆነ ሰዓት ከሁለቱ አንዱ ወደ ውጭ ማየት ይጀምራል። ይህ ደግሞ ጋብቻን ለአደጋ ያጋልጣል። ቃልኪዳንን ያስፈርሳል። ታማኝነትን ያስረሳል።

የወሲብ ህይወትን በማደስና እንደድሮም ጣፋጭ ለማድረግ ዘዴዎችን በማፈላለግ ትዳር እንዳይፈርስ ማድረግ ይቻላል።

እሷን እንደሚስትህ ብቻ አትያት። እርግጥ ነው በህግ ያገባሃት ሚስትህ ነች። ግን የወሲብ ህይወታችሁን ለማጣፈጥ እሷን እንደ ሚስትህ ብቻ ማየት አቁም። እንደዚያ ካደረግህ ከሷ ጋር ለዘላለሙ ከርቼሌ የገባህ አድርገህ ራስህን ከማየት ትቆጠባለህ። ስለሆነም እሷን ከሚስትነት ባሻገር የወሲብ ንግስትህ እንደሆነች ቁጠራት። መንገድ ላይ እንዳየሃት ቆንጆ ልጅ ባምሮህ ቅረጻት። በአዕምሮህ ያልሆነችውን ነች ብለህ ሳል። እሷም እንደዚያው። የተለያዩ ገጸባህርያትን ተላብሳቹ አብራችሁ ተውኑ። አዳዲስ የአወሳሰብ ዘዴዎችን ሞክሩ። በየጊዜው ለየት ወዳለ ቦታ ይዘሃት ሂድ። ከልጆች ከጓደኛ ከዘመድ ከሥራ ርቃችሁ ለብቻችሁ ጥሩ ጊዜን አሳልፉ። ቤት ስትሆኑ ደግሞ ክፍላችሁን የግላችሁ አድርጉት። ልጆቻችሁን ከክፍላችሁ ውጭ አግኟቸው።

ፒጃማ ለብሰህ አትተኛ። አንቺም እንዲሁ። ሰዎች ከተጋቡ በኋላ ፒጃማ ለብሰው መተኛት ያዘወትራሉ። አይታወቃቸውም እንጂ በቆየ ቁጥር የወሲብ ፍላጎታቸውን ይቀንሳል። ሁሌም ፒጃማ እየለበስክ የምትተኛ ከሆነ እንደድሮው ማራኪ ሆነህ አትታያትም። ዕድሜዋ እየገፋ መምጣቱን ነው የምታስታውሳት። ሳትጋቡ በፊት የነበረህን የአልጋ ውስጥ ባህሪ ብዙም አትቀይር። በፓንት (ቦክሰር) ብቻ ከነበረ የምትተኛው አሁንም በፓንት ብቻ ተኛ። እሷ የምትወደውን ከነቴራ ለብሰህ ከነበረ የምትተኛው አሁንም ያንኑን ከነቴራ የሚመስል ለብሰህ ተኛ። ፒጃማ ደራርበህ የምተኛ ከሆነ ግን አንተም እንቅልፍ ይወስድሃል እሷም የወሲብ ፍላጎቷ አይቀሰቀስም።

ከሁሉም በላይ ጋብቻን ከሌላው ግንኙነት የሚለየው ዘላቂነቱ አስተማማኝ መሆኑ ነው። ስለሆነም ባለቤትህን ልታምናት ይገባል። እሷም አንተን ልታምንህ ይገባል። እናም የወሲብ ምኞትህንና ፋንታሲህን ሳትደብቅ ንገራት። እሷም የራሷን ፋንታሲ ትንገርህ። ከዚህ በኋላ የሚቀረው ነገር ፋንታሲያችሁን በፈለጋችሁት ሰዓት እውን ማድረግ ነው። ፋንታሲህን እውን ካደረገችልህ አንተም የሷን እውን ካደረግህላት ሌላ ፍለጋ ሾልኮ መውጣቱ የማይታሰብ ይሆናል። የማትተማመኑና የወሲብ ፍላጎታችሁን ግልጽ አውጥታችሁ የማትወያዩ ከሆነ የወሲብ ወላፈናቹ ሳይቆይ እየተዳፈነ ይሄዳል ትዳራችሁም መቀዝቀዝ ይጀምራል።

2 thoughts on “ወሲብና ትዳር

  1. Really I like it this site and it is interesting. But please just post what is favorable to Ethiopians and not to be under control of Western societies. If it is possible for you make it understand able in Ethiopian context.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s