ወንዶችና የወር አበባ

አንድ አንባቢ ስለ የወር አበባ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የሚከተለው ትንታኔ ቀርቧል።

ኢትዮጵያ ውስጥ (ኤርትራንም ጨምሮ) ከወሲብ ቀጥሎ ሌላ እንደ ታቡ የሚታየው ነገር፣ የሴቶች የወር አበባ (ሜኑስትሬሽን ወይም ፔሬድ) ነው። የወር አበባ እንደ ታቡ እንዲታይ ከፍተኛ ሚና ከተጫወቱት ተዋንያኖች መካከል ሐይማኖት ዋነኛው ነው። ሐይማኖት የወር አበባን እንደ መጥፎና አጸያፊ ነገር–እንደ ጉድፍ–እንድናየው አስገድዶናል። የወር አበባ የምታየውንም ሴት (እናታችንን፣ እህታችንና ጓደኛችንን ጨምሮ ማለት ነው)፣ የወር አበባዋ እስኪቆም ድረስ እንደ ቆሻሻ እንድናያትና ሳትነጻ “የተቀደሰ ቦታ” እግሯ መርገጥ እንደሌለበት ያስተምረናል። ሳይንሳዊ ያልሆነው ሐይማኖታዊ ትንታኔ፣ የወር አበባ አመጣጥን እንደ መርገምት ስለሚቆጥረው፣ እኛም ለወር አበባ ያለን አመለካከት ከእርግማን የተለየ አይደለም። ስለሆነም ሴቶች የወር አበባቸው ሲመጣ ሴት መሆናቸውን ለመርገምና ወይም ለመጥላት ይገደዳሉ። በዚህ አስቸጋሪ ሰዓት፣ ፍቅር ሰጥቶ ከጎናቸው የሚሆን ወንድ ጥቂት ነው።

ሐይማኖት ስለወር አበባ የሚሰጠውን ገለጻ በተመለከተ ለአብነት ያህል የሚከተሉትን ጥቅሶች እንመልከት፦

ቅዱስ ቁርዓን፦

“የወር አበባ አጸያፊ ነው። ሴቶችን በወር አበባ ጊዜ ራቋቸው። ንጹህ እስከሚሆኑ ድረስ አትቅረቡዋቸው። ንጹህ በሆኑም ጊዜ አላህ ባዘዛችሁ ሥፍራ ተገናኟቸው። አላህ (ከኃጥያት) ተመላሾችን ይወዳል በሏቸው።” (አል በቀራ 222)

መጽሐፍ ቅዱስ፦

“ሴት ጊዜውን እየጠበቀ የሚመጣው የደም መፍሰስ ቢኖርባት፣ የወር አበባዋ ርኵሰት እስከ ሰባት ቀን ይቆያል፤ በዚህ ጊዜ ማንም ሰው ቢነካት እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። በወር አበባዋ ጊዜ የምትተኛበት ማንኛውም ነገር ርኩስ ይሆናል፤ የተቀመጠችበትም ነገር ርኩስ ይሆናል። መኝታዋን የነካ ማነኛውም ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል። … አንድ ሰው ከሷ ጋር ቢተኛና የወር አበባዋ ቢነካው፣ እስከ ሰባት ቀን ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ እርሱ የሚተኛበት መኝታ ሁሉ ርኩስ ይሆናል። ሴት ከወር አበባዋ ጊዜ ሌላ ብዙ ደም ቢፈሳት፣ ወይም የወር አበባዋ ጊዜ ካለፈ በኋላ የደሙ መፍሰስ ባይቋረጥ፣ ልክ እንደ ወር አበባዋ ጊዜ፣ ደም መፍሰሱ እስኪያቆም ድረስ ርኩስ ትሆናለች። …” (ዘሌዋውያን 15፥ 19-30)

ተፈጥሯዊ በሆነ ክስተት ላይ ይሄ ሁሉ ውርጂብኝ ሲወርድ፣ አይጣል ነው!

ብዙ ወንዶች (በተለይ የሐበሻ) ለወር አበባ ያላቸው አመለካከት፣ ላይ ከተጠቀሱት ጥቅሶች የተለየ አይደለም። ይህም ካለማወቅ የተነሳ ነው። የሚገርመው ግን ይህ ተፈጥሯዊ ክስተት በባሕላችን “የወር አበባ” ተብሎ መጠራቱ ነው። ይሄ ተቃርኖ እንዴት ሊፈጠር እንደቻለ ማጥናት አስፈላጊ ሳይሆን አይቀርም። ሐይማኖት “ጉድፍ ነው! እርግማን ነው!” ሲል፣ ባሕላችን ደግሞ “አይ፣ “የወር አበባ” መባል አለበት!” ብሎ ሲከራከር፣ ለምን አያስገርም? ነገር ግን በኛ አዕምሮ ተቀባይነትን ያገኘው የሐይማኖት ፕሮፓጋንዳ ስለሆነ፣ ተፈጥሯዊውን ክስተት ለመሰየም የባሕልን አቋም ብንቀበልም፣ ተግባር ላይ የምናውለው ግን ሐይማኖታዊ ትርጓሜውን ነው—ሐይማኖት ያን ያህል ባሕልን የማሸነፍ ኃይል አለው፤ ሳይንሳዊ እውነታን ግን ረግጦ ማለፍ አይችልም፤ ለዚህም ነው ከጊዜ ወደ ጊዜ ሰዎች ለወር አበባ ያላቸው አመለካከት እየተቀየረ የመጣው።

በተለይ አሁን ባለንበት ዘመን፣ ወንዶች ለወር አበባ ያላቸውን አመለካከት ቀይረው፣ ስለወር አበባ ግንዛቤ ለመጨበጥ ጥረት እያሳዩ ነው፤ ሴቶች የወር አበባቸውን ሲያዩ፣ “አይዞሽ፣ ከጎንሽ ነኝ፣ ምን ይሰማሻል፣ ምን ልታዘዝ?” ማለትም ጀምረዋል። ከዚያም አልፈው፣ በወር አበባ ጊዜ ወሲብ መፈጸም የሚያምራቸው ወንዶች ቁጥራቸው ትንሽ አይደለም። አንዳንድ ወንዶች ግን ዛሬም፣  አይደለም በወር አበባ ጊዜ ወሲብ ሊፈጽሙ፣ ስለወር አበባ ሲነሳ ያንገሸግሻቸዋል። “እወድሻለሁ፣ አፈቅርሻለሁ፣ እሞትልሻለሁ” የሚሏትን ሴት፣ የወር አበባዋ እስኪቆም ድረስ የሚሸሿትም አሉ። ለነገሩ ብዙ ሴቶች፣ ወንዶች ለወር አበባ ያላቸውን የተዛባ አመለካከት ስለሚያውቁት፣ የወር አበባቸው ሲመጣ፣ የሚወዱትን ወንድ ላለማስቀየም፣ የወር አበባቸው እስኪቆም ድረስ ወይ ራሳቸውን ያገላሉ አልያም “የወር አበባዬ መጥቷልና ለጊዜው አትድረስብኝ” የሚል ማስጠንቀቂያ አቅርበው ሕመማቸውን ለብቻቸው ይወጣሉ። አንዳንድ ሴቶች ደግሞ የወር አበባን እንደ መከላከያም የሚጠቀሙ አሉ። ለምሳሌ ካልበዳሁሽ እያለ በየጊዜው የሚጨቀጭቃት ወንድ ካለ፣ “የወር አበባዬ ላይ ነኝ” በማለት ከአጠገቧ አርባ ክንድ እንዲርቅ ታደርገዋለች። ብዙ ጊዜ ይሄ ቴክኒክ ለሴቶች ውጤትን ያስገኛል።

የወር አበባ መቼና እንዴት ይከሰታል?

የወር አበባ ዑደት (ሳይክል) በአማካይ 28 ቀናትን ይፈጃል። አንዳንድ ጊዜ ግን በ25ና በ35 መካከል ሊመጣና ሊሄድ ይችላል። የወር አበባ ዑደት (ሳይክል) የሚቆጠረው ደም መፍሰስ ከጀመረበት ዕለት አንስቶ ነው።

የመጀመሪያው የወር አበባ ዑደት ከ3 እስከ 5 ባሉት ቀናት ይከሰታል። ይህም የሚሆንበት፣ ከovary የተላከችው ቅንቁላል ከስፐርም ጋር ሳትገናኝ ስትቀር፣ ለጽንስ ማሳደግያነት ሲዘጋጅ የነበረው የማህጸን ግድግዳ ጥቅም ስለማይኖረው ይፈርሳል። ፍርስራሹም ከደም ጋር ተቀላቅሎ በእምስ በኩል ይወገዳል። በዚህ ጊዜ የestrogen እና progesterone ሆርሞኖች (የወሊድ ሆርሞኖች) መጠን ዝቅተኛ ይሆናል።

ሁለተኛው ዑደት ደግሞ ከ5 እስከ 14 ባሉት ቀናት የሚከሰተው ነው። በዚህ ጊዜ የestrogen መጠን ይጨምራል። የestrogen መጨመር፣ እንቁላል ስፐርምን ፍለጋ ወደ fallopian tube ጉዞ መጀመሯን ያመላክታል። ከስፐርም ጋር ሳትገናኝ ስትቀር ovulation ይካሄዳል—ይህም ማለት ልክ እንደ መጀመሪያው የማሕጸን ግድግዳ መፍረስ ይጀምራል፣ የሚከሰተውም አብዛኛውን ጊዜ በ14ኛው ቀን ነው። የovulation ሂደት ሲካሄድ የestrogen መጠን ይቀንሳል። Ovulation ከተካሄደ በኋላ፣ ሶስተኛው የወር አበባ ሂደት ይጀምራል። የማህጸን ግድግዳ እንደገና ራሱን ያዘጋጃል። በዚህ ጊዜ የሁለቱ ሆርሞኖች መጠን ከፍ፣ ዝቅ እያለ ይቀጥላል።  ሌላ እንቁላል ከovary እስኪላክ ድረስ 14 ቀናት አሉ። ከ14 ቀናት በኋላ ደግሞ፣  የሚከተለው ምስል እንደሚያሳየው፣  ዑደቱ እንደገና ይጀምራል።

ከደም መፍሰስ ባሻገር፣ ብዙውን ጊዜ ሴቶችን ለህመም የሚዳርጋቸው፣ የሁለቱ ሆርሞኖች መጠን ሳይጠበቅ ከፍና ዝቅ ማለት ነው። በተለይ የestrogen መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር ወይም መቀነስ፣ አዕምሮ ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ጥናቶች ይጠቁማሉ። ይህ ሆርሞን አዕምሮ ላይ ባለው ተጽዕኖ፣ በወር አበባ ሰሞን የሙድ መቀያየርንና የአዕምሮ ህመምን (ራስ ምታትን ጨምሮ) ያስከትላል። በሚገርም ሁኔታ ደግሞ የሆርሞኑ መጠን ሲጨምር፣ አንዳንድ ሴቶች ንቁና አንደበተ ርቱዕ ይሆናሉ። አስፍቶ የማየት ክህሎታቸውም ይጨምራል። የሆርሞኑ መጠን ሲቀንስ ደግሞ ተቃራኒው ይከሰታል። ሌላኛው ሆሮሞን (Progesterone)፣ በወር አበባ ጊዜ፣ በአዕምሮ ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ በተመለከተ እስካሁን ብዙም የሚታወቅ ነገር የለም።

ጥናት ከተደረገባቸው ሴቶች፣ ከመቶ 80ዎቹ፣ በወር አበባ ጊዜ ከስነልቦናና ከሰውነት ድካም ጋር የተያያዙ ህመሞች እንደሚሰሟቸው ተደምድሟል። የወር አበባ ሲመጣ በስፋት ከሚታዩት ምልክቶች መካከል ሆድ ቁርጠትና እምስ ውስጥ መታመም፣ ማላብ፣ ተቅማጥና የሰውነት ድክምክም ማለት፣ ራስምታትና የባሕሪ መለዋወጥ፣ መነጫነጭ፣ አንዴ መሳቅና ትንሽ ቆይቶ ማኩረፍ፣ በተቀለደ ነገር ላይ መቆጣትና የመሳሰሉት ተጠቃሾቹ ናቸው።

ብዙ ሴቶች በወር አበባ ጊዜ የሚከሰቱ ህመሞችን ተቋቁመው የለትዕለት ተግባራቸውን ያከናውናሉ። በገጠሪቱ ኢትዮጵያ በተለይ ውሃ ይቀዳሉ፣ የባሎቻቸውንና የልጆቻቸውን ልብሶች ያጥባሉ፣ እንጨት ይለቅማሉ፣ ገበያ ዕቃ ተሸክመው ይሄዳሉ ወይም ከገበያ ዕቃ ተሸክመው ይመለሳሉ፣ እንጀራ ይጋግራሉ፣ ወጥ ይሰራሉ፣ ቤት ያጸዳሉ፣ ምኑ ተወርቶ … እንዲህም ለፍተው ምስጋና ካገኙ ተመስገን ነው! አብዛኞቹ ዱላና ስድብ ነው የሚወርድባቸው። እንደ ጉድፍ ነው የሚታዩት። ባሎች የሞቀ ብርድ ልብስ ውስጥ ሲተኙ፣ እነሱ ብቻቸውን ተጠቅልለው፣ ብርድ እየጠፈጠፋቸው ሊተኙ ይችላሉ።

በወር አበባ ጊዜ ልክ እንደ ህመማቸው፣ የሴቶች የወሲብ ፍላጎትም ይቀያየራል። እንደየሴቱ ባህሪ፣ የወሲብ ፍላጎት ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል። ሴቶች በወር አበባቸው ጊዜ የሚረብሻቸውን፣ የሚጠየፋቸውን፣ የሚጨቀጭቃቸውን ወንድ ሳይሆን የሚፈልጉት፤ የሚመቻቸውን፤ የመበዳት ፍላጎታቸው ሲጨምር፣ ባይበዳቸው እንኳ ከጎናቸው ሆኖ የሚያስተዛዝን፤ ህመም የሚያስታግሱ መፍትሔዎችን የሚያቀርብ፤ የሚያዝናናቸው፤ ሲነጫነጩ የማይበሳጭ፤ ፍቅር የሚሰጣቸውን ወንድ ነው። የወሲብ ፍላጎታቸው ሲነሳሳ ለመብዳት ፈቃደኛ የሚሆነው ደግሞ የሌለ ደስታን ይፈጥርላቸዋል ምክንያቱም 1) ስሜታቸውን ስለሚያበርድ 2) ስላልተጠየፋቸው። ሆኖም ሴቶች እዚህ ላይ መገንዘብ ያለባቸው አንድ ቁምነገር አለ። አንዳንድ ወንዶች በወር አበባ ጊዜ ወሲብ ለመፈጸም ፈቃደኛ የማይሆኑት ተጠይፈው ሳይሆን የለመዱት ነገር ስላልሆነ ነው። አንድ ሰው ያለመደውን ነገር አድርግ ሲሉት መቼስ ወዲያው ፈቃደኛ አይሆንም። ከጊዜ በኋላ ሊለወጥ ይችላል። ካልተለወጠም ውሳኔውን ማክበር ተገቢ ነው። ጥሩ ተንከባካቢ ሆኖ፣ ግን መብዳት የማይፈልግ ከሆነ፣ ይቅርታ ሊቸረው ይገባል።

ወንዶች ማወቅ ያለባቸው ነገር፣ በወር አበባ ጊዜ ሴቶች የሚሰማቸው ስሜት ዩኒፎርም አለመሆኑን ነው። እያንዳንዷ ሴት የራሷ የሆነ ስሜት አላት። ከውስጧ የሚሰማትን የምታውቀው እሷ ብቻ ናት። ሁሉም ሴቶች አንድ ዓይነት የወር አበባ ታሪክ የላቸውም። ስለዚህ ያንዷን ሴት ባህሪ ሌላዋ ላይ መፈለግ አስፈላጊ አይደለም። “እዚያቺኛዋ ላይ እንዲህ አደርግ ስለነበር፣ እዚህችኛዋ ላይም ላድርገው” ከማለት መቆጠብ ተገቢ ነው። መሆን ያለበት፣ የሚሰማትን ስሜት ጠይቆ መረዳትና ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ ማቅረብ ነው። የወር አበባዋ መምጣቱን ካወቅህ፣ ህመሟ እስኪያቆም ድረስ በትዕግስትና በፍቅር ጊዜውን አብረሃት አሳልፍ።

የወር አበባን እንደ ወሊድ መቆጣጠሪያነት መጠቀም

ኢትዮጵያ ውስጥ የወር አበባ በስፋት እንደ ወሊድ መቆጣጠሪያነት ያገለግላል—በተለይም በገጠሪቱ ኢትዮጵያ። ሆኖም አስተማማኝነቱ በጣም ዝቅተኛ ነው። ስለሆነም ሳይታሰብ ወይም ሳይታቀድ ልጅ የሚጸነስበት ጊዜ ብዙ ነው። ይህም የሚሆንበት ምክንያት ovulation ከመካሄዱ በፊት ያለው ጊዜ በጣም አደገኛ በመሆኑ ነው። ይህ የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል። እርግዝናን መቶ በመቶ አይከላከልም። ከአባላዘር በሽታዎች አያድንም።

ለብዙ ሰዎች፣ የወር አበባን መሰረት ያደረገ የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴ ጠቃሚ መስሎ የሚታይበት ምክንያት፦ 1) በተለምዶ ተቀባይነትን ስላገኘ (በተለይ እንደ ገጠር ባሉ አካባቢዎች) 2) በወሲብ ጊዜ ከኮንዶምና ከመሳሰሉት የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴዎች ጣልቃ ገብነት ስለሚገላግል ነው።

2 thoughts on “ወንዶችና የወር አበባ

  1. ዝርክርክ የሃይማኖት አስተሳሰብ ሁሌም ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል:: ጥሩ ፅሁፍ ልክ አንደ ተለመደው::
    የወር አበባ ሚስቴ ስታይ ወደ ሴጋ አመለሳለሁኝ ቅቅቅ::

  2. የሠው ልጅ ጣፋጭ ምግብ ተመግቦ ቆሻሻ እንደሚያስወጣ ለማንም ግልጽ ነው፤፤ ስለዚህ ይህን ተፍጥሯዊ ቆሻሻ ብሎ መጥራት ውርወጅብኝ ማውረድ አይደለም፡፡ እንደ ኢስላም ሃይማኖት ሴትን ቆሻሻ ብሎ አልሰደበም፡፡ ነገር ግን የወር አባባው ቆሻሻ በመሆኑ በግንኙነት ወቅት እንድንርቀውና ግንኙነት ማድረጉ ፀያፍ መሆኑን አዋቂው፣ ጥበበኛው፣ ኃያሉ፣ ሁሉን ቻዩና ታጋሹ አምላክ አላህ ያዘዘን፡፡ አምላክ ፍጹም አዋቂ የሆነ ጌታ ነው፡፡
    ግን ማህይም እንደወንከ ግልጽ ነው፡፡ ዓላማህ ከነጮች ከተማርከው ሠይጣናዊ ትምህረት ጣፋጭ በሚመስል ፅሁፍህ ሠዎችን ወደ ጥፋት ለመክተት የምታደርገው ጥረት ምን ያህል የክፋት አሽከር መሆንህን እያስመሰከርክ ነወ፡፡
    ኢስላም ስለሴቶች ምን አይነት አቋም እንዳለው፣ ወሲብ ያስከተለውንና እያስከተለ ያለው የታሪክ ውድቀት ለማወቅ ከፈለክ በአማረኛ የተተረጎመ ‘’ሴቶች በኢስላም’’ የሚል መጽሃፍ ጋብዥሃለው፡፡ ለአንባቢዎች ጭምር፡፡ ይህን ከፉ አስተሳሰባቸሁን በዲሞክራሲ ስም ለመጫን ዓለምን ትበጠብጣላቸሁ፡፡ የሸሪዓ ህግን የምትጠሉት በዚህ ክፉ አስተሳሰባቸሁ ነው፡፡ አላህ ማስተንተኛ ልቦና ይሥጥህ! ከተንኮልህ ይጠብቀን! አሚን!!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s