እንደምትወድህ እንዴት ታውቃለህ?

ሰላም፣ ሰላም ውድ አንባቢዎች!

እንድምን ከረማችሁ? እኛ እንደ መስቀል ወፍ ጠፍተንም ቢሆን ይኸው ብቅ ብለናል። ለብዙ ጊዜ ከድረገጹ ብንርቅም በሐሳብ ግን ሁሌም አልተለየነውም። እናም ዛሬ አዲስ መጣጥፍ በሴት አምደኛችን ለወንዶች ምክር ይዘን ከች። አንብባችሁ አስተያየትና ጥቆማ ከመስጠትና ጸሃፊዋን ከመደገፍና ከማረም አትቆጠቡ። መልካም ንባብ!

እንደምትወድህ እንዴት ታውቃለህ?

እንበልና የሴት ጓደኛ አለህ። በጓደኝነት ደረጃ እያላችሁ ሲውል ሲያድር ወደድካት። ቆየህና አፈቀርካት። ለመናግር ግን ድፍረቱ የለህም ምክንያቱም ፈሪ ሆነህ ሳይሆን የሷን ስሜት ስለማታውቅ። ትውደድህ አትውደድህ እንዴት ልታውቅ እንደምትችል በዚህ ጽሁፍ ልረዳህ እሞክራለሁ። አሁን በቁላህ ሳይሆን ባምሮህ የምታስብበት ሰዓት ነው። ስለዚህ በጽሞና ተከታተለኝ! ከወንዶች ይልቅ ከኔ ከሴትዋ የምትሰማው ምክር የተሻለ ነው ብዬ አምናለሁ።

አንድ ወንድ አንዲት ሴት ትውደደው አትውደደው እንዴት ሊያውቅ ይችላል? ከባድ ጥያቄ ይመስላል አይደል? አይዞህ የሮኬት ሳይንስ ግን አይደለም።

ማስጠንቀቅያ፦ ይህ መጣጥፍ ሁሉም ሴቶች ላይ የሚሰራ መምሪያ አይደለም። የአንዷ ሴት ባህሪ ከሌላኛዋ ይለያል። ስለዚህ እዚህ የምታነበውን ነገር ይዘህ ብቻ አትሩጥ። ያየሃት ሴት ሁሉ አንድ ዓይነት ባህሪ አላት የሚል አስተሳሰብ ካለህ አንተ ዶማ ነህ።

እኛ ሴቶች ስሜታችንን የምንገልጽባቸው የተለያዩ መንገዶች አሉ። ግልጽ ሆነን ከመቅረብ ይልቅ ስሜታችንን እንድንደብቅ የሚያስገድዱን ምክንያቶችም አሉን።

አንድ ሴት ያይን ፍቅር ያዛት እንበል። ወይም የወሲብ አምሮት መጣባት። ይህን ስሜቷን እንዴት ነው ለተመኘችው ወንድ የምትገልጸው?

መቼም እንደምታውቁት አብዛኛው የሀገራችን ባሕል ሴቶች አይደለም ስለስሜታቸው ስለቤተሰብ ጉዳይ እንኳን አፍ አውጥተው ቤት ውስጥ እንዲወያዩ ብዙም አይፈቅድም። በዚህ ባሕል ያደግን አብዛኞቻችን ሴቶች ደግሞ ስሜታችንን የመግለጽ ችግር አለብን። ሌላው ሴት ሳትሆን ወንድ ቀድሞ ስሜቱን መግለጽ አለበት የሚለው አቋም በሀገራችን ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አለማት ጎልቶ የሚታይ ጉዳይ ነው። ይህ ጉዳይ በራሱ ሴቶች ላይ ተጽኖ ያሳድራል።

ስሜትዋን ሳትፈራ የምትገልጽን ሴት እንደ ዓይን አውጣ ወይም ስድ አደግ ወይም ዝሙተኛ አድርገው የሚቆጥሩ ብዙዎች ናቸው። እንግዲህ እኛ ሴቶች ብዙውን ጊዜ ደፍረን ስሜታችንን የምንገልጸው ከዚህ ሁሉ ፈተና አልፈን ነው።

ከባህላዊ ውጭ ደግሞ ስሜትቻንን እንዳንገልጽ የሚያደርገን ምንድነው? አንድን ወንድ ከወደድኩት ደፍሬ እንደምወደው እንዳልነግረው የሚያደርገኝ ምንድነው?

አብዛኞቻችን ፍራቻ አለን። ፍራቻው በብዙ መልኩ ቢገለጽም የሚከተለውን ይመስላል። ለምሳሌ ጀማል ከሚባል ልጅ ጋር ፍቅር ያዘኝ። ጀማል አብሮኝ የሚማር ልጅ ነው እንበል። ያውቀኛል ግን እንደምወደው አያውቅም። እናስ እንደምወደው ብነግረው ምን ሊከሰት ይችላል? የፍራቻዬ ምንጭ ያለው እዛ ላይ ነው።

ጀማልን ወደድኩህ ብለው

አንደኛ፦ ያልጠበቀው ነገር ከሆነ ሊደነግጥና ውዴታዬን ላይቀበለው ይችላል። በረገገ ማለት ነው! በሬ!

ሁለተኛ፦ የጠበቀው ነገር ከሆነ ነገር ግን እሱ ግን ለኔ ስሜት ከሌለው እስኪበዳኝ ድረስ እኔም እኮ ወድሻለሁ ብሎ ዋሽቶ ስሜቱን ካረካ በሁዋላ ውዴታዬን ገደል ሊከተው ይችላል። እንዲዚህ ዓይነት ጀማሎችን ምን እንደማደርጋቸው ታውቃለህ? ኩላሊታቸውን ነው የምጨፈልቅላቸው!

ሶስተኛ፦ ጀሙዬ የኔ ምስኪን እሱም ለኔ ስሜት አለው እንበል። በደስታ ውዴታዬን ይቀበለዋል ግን ቀድሜ ስለነገርኩት ኩራት ሊሰማው ይችላል። እንዲህ ዓይነቱን ኩራተኛ ደግሞ ልቡ ውስጥ ከገባሁ በኋላ ከልቡ ጋር ዳማ መጫወት ደስ ይለኛል። ብድር በምድር!

ወ.ዘ.ተ.

እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው እንግዲህ ጥቂቶቹ የፍራቻዬ ምንጮች ናቸው። እነዚህን ፍራቻዎች በውስጤ ይዤ እንዴት ነው ስሜቴን ራሴን ላደጋ ሳላጋልጥ የምገልጸው? እዚህ ጋር ነው ሚስጥሩ! እናም አዳምጥ!

የተለያዩ ምልክቶችን አሳያለሁ። ወሳኙ ግን አንተ ነህ!

አንድን ሴት እንደምትወድህ ልታውቅ የምትችለው እንደምትወዳት ስትገልጽላት ነው። እኔ የምሰጥህን ምልክቶች ተከትለህ ግልጽ ሆነህ ልታቀርበኝ ይገባል። አንተ አጠገብ መሆን የሚመቸኝ ከሆነና አንተም ለኔ ስሜት አለህ ብዬ የማስብ ከሆነ ቀስ በቀስ በሬን እየከፈትኩልህ መጣለሁ። ካንተ የሚጠበቀው ከላይ የጠቀስኳቸውን ፍራቻዎቼን እውን ሳታደርግ በከፈትኩልህ በር ሰተት ብለህ መግባትና ልብህን ለልቤ መስጠት ነው። ቀላል ነው አይደል? ለዛም እኮ ነው ሮኬት ሳይንስ አይደለም ያልኩህ! በል ሂድና የምትወዳትን ልጅ በፍቅር ቀርበህ እንደምትወዳት ንገራት። ፍቅርህን ግለጽላት። ከወደደችህ ያለምንም ጥርጣሬ ትቀበልሃለች። እሷ ቀድማ ስሜቷን ከገለጸችልህ ደግሞ እንደ ዓይን አውጣ አትያት!

ከሁሉም ነገር በላይ ቀድመህ በቁላህ አታስብ! ለመብዳት ብቻ አትንሰፍሰፍ!

7 thoughts on “እንደምትወድህ እንዴት ታውቃለህ?

  1. It is my first day watching this website and it is really helpful for those who have a problem of expressing their feelings and eager to know more about sex and its excitement!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s