“ምን ይሻለኛል?”

ሰላም፣ ሰላም ውድ አንባቢዎች!

ሳንጦምር 3 ዓመት አለፈን። በጣም ጠፋንባችሁ አይደል? እንደናፈቃችሁን ተስፋ እናደርጋለን። ይህን ጦማር ስንጀምር ሰባት ሰዎች ነበርን። ዛሬ ግን በተለያዩ ምክንያቶች ቁጥራችን ቀንሶ ሦስት ብቻ ቀርተናል።

ዴቭ፣ ነፃነትና ሶፊ።

ከብዙ ቆይታ በኋላ ለመጦመር ስንመለስ በመጀመርያ ያደረግነው እናንተ የተዋችሁልን ጥያቄዎች ማንበብ ነበር። እነዚህን ጥያቄዎች ተከፋፍለን ምላሽ ይዘን ቀርበናል።

ዛሬ የምጽፍላችሁ ሶፊ ነኝ። በርዕሱ የምታዩትን ጥያቄ ለመመለስ ብቅ ብያለሁ።

አንድ አንባቢያችን “ሴት ባየሁ ቁጥር ቁላየ እየቆመ አስቸግሮኛል። ምን ይሻለኛል?” የሚል ጥያቄ አንስቷል።

የኔ መልስ አጭር ነው።

1ኛ – የጻፍከው ነገር ለሴቶች ስድብ ነው። ምን ያህል ለሴት ልጅ ክብር እንደሌለህ ያሳያል። የሴትን ልጅ ባየህ ቁጥር ቀድሞ የሚታሰብህ ወሲብ ከሆነ ችግር አለብህና የስነልቦና ህክምና ጠይቅ። የሴት ልጅ ያንተ ቁላ ማስነሻ ዕቃ አይደለችም። ክብር ያላት ፍጡር ነች። ስለዚህ ራስህን ገምግም።

2ኛ – ቁላህን ቆንጥጠው። ስሜትህን ልትገዛው እንጂ ስሜትህ ሊገዛህ አይገባም። በጭንቅላትህ ሳይሆን በቁላህ ብቻ እያሰብክ ስለሆነ ራስህን ግዛ።

3ኛ – እህት አለህ? የሴት ዘመድስ አለህ? እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ። የሆነ ወንድ “እነዚህ ዘመዶችህን ባየሁ ቁጥር ቁላዬ ይቆማልና ምን ላድርግ” ቢልህ ምን አድርግ ብለህ ትመክረዋለህ? ያዙኝ፣ ልቀቁኝ፣ እገድለዋለሁ እንደምትል እርግጠኛ ነኝ። ያንተንም ሁኔታ በዚሁ መልኩ እየውና ራስህን ታዘበው።

በነገራችን ላይ እንዳንተ ያሉ ወንዶች እንደዚህ ዓይነት ሐሳብ የምታስቡት ሴትን ልጅ ከወሲብ ማርኪያነት ውጭ አርቆ የሚያስብ አዕምሮ ስለሌላችሁ ነው። ያቺ የምታያትና ቁላህ የሚቆምላት ሴት ግን የሌላ ሰው እህት፣ እናት፣ አክስት፣ ሚስት፣ ፍቅረኛ፣ ጓደኛ፣ ጎረቤት፣ ልጅ ነች። በወሲብ ዕቃነቷ ሳይሆን በሰውነቷ እያትና አክብራት። በህይወቷ ለማሳካት የምትፈልጋቸው ነገሮች ምን እንደሆኑ ለማወቅ ጣር። ያቺ ሴት ከወሲብ ቀስቃሽ ገላዋ በፊት የሚያስብ አዕምሮና የሚያፈቅር ልብ የያዘች ሰው መሆኗን ተረዳ። ያኔ በሰውነቷ ልትተዋወቃት ትችላለህ። ሴትነቷን ካከበርክ ማን ያውቃል ወዳህ ተዋዳችሁ ልብህ እስኪወልቅ ድረስ ልተበዳህ ትችላለች። ቅድሚያ ግን ማንነቷን ከወሲብ ጋር ብቻ አታያይዝ።

4ኛ – የምታስበው ነገር ሁሉ ወሲብ ብቻ ከሆነ የሴተኛ አዳሪዎች አሉልህ። እነሱንም ቢሆን ልታከብራቸው ይገባል። ሰውነታቸውን ስለሚሸጡልህ ከሰውነት በታች ልታያቸው አይገባም። ኤድስንና ሌሎች በወሲብ የሚተላለፉ በሽታዎችንም አትርሳ!

ህይወትህን ስለወሲብ ብቻ እያሳሰብክ ቀፎ አታድርገው።

ሶፊ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s